






የክፍለ ከተማው ከፍተኛ ኃላፊዎችና የወረዳው አመራሮች በተገኙበት በዚህ የርክከብ ስነ ስርዓት ላይ አቶ ብንያም መስፍን ( የብርሃን ባንክ ቺፍ ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስና ማርኬቲንግ ኦፊሰር) መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት ከዳር እንዲደርስ ከልደታ ክፍለ ከተማ ለቀረበው የትብብር ጥያቄ መልስ በመስጠት ጉልህ ሚና የተጫወቱትን የባንኩን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤርምያስ ተፈራን ያመሰገኑ ሲሆን በተቀመጠለት ጊዜ ውስጥ ዕድሳቱ ተጠናቅቆ ለተጠቃሚዎች እንዲተላለፍ ከፍተኛ ርብርብና አስተዋጽኦ ያደረጉትን የክፍለ ከተማውንና የወረዳውን ኃላፊዎች እንዲሁም የባንኩን ባለሙያዎች ከልብ አመሰግነዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ቤት ለታደሰላቸው ወገኖች በብርሃን ባንክ ማኔጅመንት ስም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። በመጨረሻም ባንካችን የማኅበረሰብ አቀፍ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።