የተከበራችሁ የብርሃን ባንክ ባለአክሲዮኖች

የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 እንዲሁም ለሕዝብ የሚሸጡ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ግዑዝ-አልባ ማድረግ መመሪያ ቁጥር 1047/2017 ተከትሎ ብርሃን ባንክ የባለአክሲዮኖቹን የቅርብ ግዜ መረጃ በመሰብሰብ ላይ ይገኛል። ይኽንን መረጃ በባንኩ የአክሲዮን ክፍል እና በቅርንጫፎቻችን  በአካል በመገኘት ለሰጣችሁን ባለአክሲዮኖች ምስጋናችንን እያቀረብን፣ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መረጃዎች ያላቀረባችሁ፣

ሀ. የግል አክስዮን ባለቤቶች
1.      የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (FAN) ቁጥር እና
2.      የመኖሪያ አድራሻ (ክልል፣ ከተማ፣ ክ/ከተማ&፣ ወረዳ፣ ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር እና ኢ-ሜል)

ለ. የድርጅት አክስዮን ባለቤቶች
1.       የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number)
2.      የምዝገባ ቁጥር እና
3.      የድርጅቱ ወኪል የሆነ ግለሰብ ሙሉ መረጃ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (FAN) ቁጥር እና
የመኖሪያ አድራሻ (ክልል፣ ከተማ፣ ክ/ከተማ&፣ ወረዳ፣ ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር  እና ኢ-ሜል))
ወደ ባንኩ የአክሲዮን ክፍል፣ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ወይም በቴሌግራም +251974013820 መረጃዎን በመላክ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲያሳዉቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ  0116-62-34-21/0116-61-65-97 ይደውሉ ወይም የብርሃን ባንክ  ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ @berhanbanksc ይከታተሉ፡፡

እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!
ብርሃን ባንክ አ.ማ