ብርሃን ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንስ ተቋማት መናሀሪያ በሆነው ሜክሲኮ አካባቢ በ 5400 ሜ.ካ ቦታ ላይ የዋና መስሪያቤት ህንጻ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ፡፡

የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነስርዓቱ አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገ/ሥላሴ፤የብርሀን ባንክ የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጉማቸው ኩሴ፤ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ግሩም ጸጋዬን   ጨምሮ የባንኩና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ፤ ባለ አክሲዮኖች እና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡

አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገ/ሥላሴ በስነ ስርአቱ ላይ ልክ እንደስሙ ባንኩ በብርሀን ፍጥነት ህንጻውን ገንብቶ ማጠናቀቅ አለበት ሲሉ  አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ባንኩ የሚገነባው የዋና መስሪያቤት ህንጻ  ለባንኩም ሆነ ለሃገራችን ሀብትን ከመፍጠር ባለፈ ለደንበኞች ዘመኑ የሚጠይቀውን ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችልው ይሆናል፡፡

ባንኩ በስፍራው ደረጃውን የጠበቀ ህንጻ በመገንባት ለከተማዋ ውበትና መልካም ገጽታ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት አሻራውን እንደሚያኖርም ተገልጸዋል፡፡