ብርሃን ባንክ በወላይታ ሶዶ ከተማ የባንኩ ከፍተኛ የሰራ ኃላፊዎች እና የክልሉ ት/ቢሮ በተገኙበት ቅዳሜ ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም
በዓይነቱ ልዩ የሆነውን የተማሪዎች የክፍያ መተግበርያ ዘዴ (School pay ) በያቆብ ሆቴል ከ60 በላይ ለሚሆኑ ት /ቤቶች አስተዋወቀ ፡፡
በዚህ ፕሮግራም ላይ ከፍተኛ የባንኩ የስራ አመራሮች እና የክልሉ የትህምህርት ቢሮ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን የተማሪዎችን
የክፍያ መተግበርያ (school pay ) ዘዴ በባንኩ የዲጅታል እና የፋይናሻል ዳይሬክትር በሆኑት በአቶ ፈየራ ኤጃታ
ከት/ቤትች እና ከክልሉ ት/ቢሮ ለመጡ ተሳታፊዎች ገላጻ ያደረጉ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
በዚህ በመቀጠል በክልሉ ከ1900 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ያ ለው የቤዛኤል ት/ቤት የፋይናስ ሀላፊ የሆኑት አቶ ኤፍርኤም መንግስቱ ብርሃን ባንክ በክልሉ እያስተዋወቀ ያለው የተማሪዎች ክፍያ መተግበርያ ዘዴ በት/ቤቱ ያለውን የክፍያ ዘዴ ያዘመነ ከመሆኑ መተጨማሪ ለወላጆች እና ለት/ቤቱ አሰራር ላይ ከፍተኛ አገዛ እንዳደረገ ገለጻዋል ፡፡
አያይዘውም የክልሉ የት/ም/ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታደሰ ኩማ በማጠቃለያ ንግግራቸው እንደገለጹት ብርሃን ባንክ የተማሪዎች የክፍያ ዘዴ በጣም ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ት/ቤቶችን እና ለወላጆች በቀላሉ ከተማሪዎች የክፍያ ዘዴ ከመፈጸም በተጨማሪ አጠቃላይ የት/ቤቶች እና ወላጆች ግንኙኘትን ያቀራረበ ቴከኖሎጂ ነው ብለዋል፡፡