አስተማማኝነት እና ሃቀኝነት!
የብርሃን ባንክ ዋና መርሆች ናቸው።

ብርሃን ባንክ ለደንበኞቹ አስተማማኝ እና ሃቀኛ የሆኑ የባንክ አገልግሎቶችን በመስጠትና ተደራሽነቱን በማስፋት ውጤታማነቱንና ትርፋማነቱን እያስቀጠለ ይገኛል።
ባንካችን ያስቀመጠውን ራዕይና ተልዕኮ ማሳካት እንዲያስችለው የአጭር ጊዜ የስትራቴጂክ ዕቅድ ነድፎ እየሰራ ሲሆን በዚህም የኮር-ባንኪንግ ሲስተም ማሻሻያ ሥራዎችን በማድረግ ዘመኑ የሚፈልገውን የዲጂታል አገልግሎት ለደንበኞቻችን መስጠትን ተቀዳሚ ዓላማው አድርጓል። በተጨማሪም ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ያለውን ተቋማዊ ሚና ከፍ በማድረግ እና ግብርን በታማኝነት በላቀ ደረጃ በመክፈል የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል!
እንዲሁም በተለያዩ የማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ በሚገባ በመሳተፍ ለህዝብ አለኝታነቱን አሳይቷል፤ ከነዚህም ውስጥ፡- በተለያዩ ጊዜያት እንደ አረንጋዴ አሻራ ያሉ ሀገራዊ መርኃ ግብሮች ላይ ምላሽ በመስጠት እና በተለያዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ጊዜ ከህዝብ ጎን በመቆም አጋርነቱን እያሳየ ይገኛል።
ይህም የባንካችንን ውጤታማነት የሚያሳይ በመሆኑ ኩራት የተሰማን ሲሆን በቀጣይም ለደንበኞቻችን ተደራሽና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት እና ከማህበረሰባችን ጎን በመቆም ውጤታማነታችንንና ሀገራዊ ኃላፊነታችንን እንደምናስቀጥል እያረጋገጥን፡ የብርሃን ቤተሰብ በመሆን ቀላል እና ምቹ አገልግሎት ያግኙ፡፡