ብርሃን ባንክ በሁለተኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ግኝት ማበረታቻ ሽልማቶቹን ለእድለኞቹ አስረክቧል፡፡

ብርሃን ባንክ በሁለተኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ግኝት ማበረታቻ ሽልማቶቹን ለእድለኞቹ አስረክቧል፡፡ በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ የብሄራዊ ሎተሪ አመራሮች እና ታዛቢዎች በተገኙበት የዕጣ ማውጣት ስነስርዓቱ ከተከናወነ በኋላ የእድለኞቹ ዝርዝር ተለይቶ ለባንኩ እንደተላከ የባንኩ ከፍተኛ አመራር አካላት በተገኙበት የሽልማት ርክክቡ ሰኞ መስከረም 12 ቀን 2012 ዓ.ም በደማቅ ስነስርዓት ተከናውኗል፡፡ በርክክቡም ወቅት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም አላሮ ሽልማቶቹን ለእድለኞቹ ባስረከቡበት ወቅት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ባንኩ በእቅዱ መሰረት ከፕሮግራሙ ሊያገኝ ያለመውን ያሳካ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ባንኩ ለወደፊቱ መሰል ፕግራሞችን በማስቀጠል ደንበኞችን ባለእድል በማድረግ ከፕግራሞቹ ባንኩ የሚገባውን ማግኘት እንደሚቀጥል ያለቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰሎሞን አሰፋ በበኩላቸው ለደንበኞች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ደንበኞች የ2012 ዓም አዲስ ዓመትን በአሸናፊነት ስሜት መጀመራቸው መልካም መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከተሸላሚዎቹ በወቅታዊ ዋጋው የአንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ ብር ዋጋ የሚያወጣ ዘመናዊ አይሱዙ የጭነት መኪና  አሸናፊ የሆኑት የ75 ዓመቷ ወ/ሮ ውበቴ ታደሰ አሸናፊ ያደረጋቸውን አጋጣሚ ሲያስታውሱ ልጃቸው ከውጭ ሃገር የላከችላቸውን የ100 የአሜሪካን ዶላር ከብርሃን ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ተቀብለው የካርድ ስጦታ ተበርክቶላቸው መሄዳቸውን እንደሚያስታውሱ ገልፀው በቅርቡ ደግሞ ተድውሎላቸው በዚያው ዕታ የዚህ ዘመናዊ መኪና አሸናፊ መሆናቸው በስተርጅና እድሜያቸው መጦሪያ የሚሆን ቋሚ ቅርስ እንዳገኙ እንደሚሰማቸው ነው በደስታ ስሜት የተናገሩት፡፡ ሌሎች ሶስት የባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪዎች፣ 10 ባለ 32 ኢንች ሳምሰንግ ኤል ኢ ዲ ቴሌቪዢኖች እንዲሁም 10 ስማርት ሳምሰንግ የሞባይል ስልኮች የሽልማቶቹ አካል ሲሆኑ አብዛኛዎቹ አሸናፊዎች ሽልማቶቻቸውን በወቅቱ የተረከቡ ሲሆን ደስታቸውን በመግለፅ ለወደፊቱም በተሻለ መንገድ ከባንኩ ጋር ሊሰሩ እንደሚፈልጉ ቃል ገብተዋል፡፡

 Demos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up