ብርሃን ባንክ አ.ማ. አዲስ የቦርድ ሊቀመንበርና ም/ሊቀመንበር ሰየመ

ብርሃን ባንክ አ.ማ.  አዲስ የቦርድ ሊቀመንበርና ም/ሊቀመንበር ሰየመ

ብርሃን ባንክ አ.ማ. አዳዲስ የቦርድ አመራሮችን ምርጫ በባለአክስዮኖች ኅዳር 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሔዱት 8ኛ መደበኛ እና 4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በተካሔደው መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክም የምርጫ ውጤቱን ተቀብሎ የካቲት 2 ቀን 2010 ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር ፋኢሱ/ገሱዳ/127/18 አፅድቋል፡፡ የባንኩ ተመራጭ ቦርድ አባላትም የባንኩን የቦርድ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ሰይመዋል፡፡

በዚህም መሰረት ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ብርሃን ባንክ አ.ማ. በቦርድ ሊቀመንበርነት እንዲመሩ የተመረጡት አቶ ጉማቸው ኩሴ ናቸው፡፡ በምክትል ቦርድ ሰብሳቢነት ደግሞ ዶ/ር ናርዶስ ብርሃኑ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

አዳዲስ አባላቶች

 1. ጉማቸው ኩሴ                                  ሊቀመንበር
 2. ዶ/ር ናርዶስ ብርሃኑ                      ም/ሊቀመንበር
 3. አርክ. ዳንኤል አሰፋ                       አባል
 4. አቶ ሙላቱ በላቸው                        አባል
 5. ዶ/ር ፋሲል ናሆም                         አባል
 6. ወ/ሮ ሜሮን ገዛህኝ                         አባል
 7. ወ/ሮ ሜላትወርቅ ሀይሉ                አባል
 8. ወ/ሮ አማረች በካሎ                       አባል
 9. ዶ/ር አይናለም አባይነህ                አባል
 10. አቶ አለማየሁ መለሰ                      አባል
 11. አቶ ኢሊጎ ለገሰ                              አባል

                                                                        ብርሃን ባንክ አ.ማ.  2 Comments

 • winta tekla zeray

  i want make account in your bank haw i live in riyadh

 • Yonas

  ስለጥያቄዎ እናመሰግናለን!
  የብርሃን ባንክ አካውንት ለመክፈት ሁለት መንገዶች ሊከተሉ ይችላሉ
  አንደኛ በአካል መጥተው መክፈት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ካሉበት ሀገር በሚገኝ ኤምባሲ በኩል ኢተዮጵያ ውስጥ ለሚኖር ሰው ውክልና በመስጠት ተወካዩ ግለሰብ በርስዎ ስም ሂሳብ መክፈት እና ቁጠባዎትን ማንቀሳቀስ ይችላል፡፡ እርስዎም ወደ ሃገርዎ ሲመለሱ ማንቀሳቀስ ይችላሉ፡፡

Leave a Reply

Demos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up