ብርሃን ባንክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ሁለገብ ህንጻ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ፡፡

ብርሃን ባንክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ሁለገብ ህንጻ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ፡፡
የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነስርዓቱ፤ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ግሩም ጸጋዬ እና የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙን ጨምሮ የባንኩና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ አመራሮች እና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡
ባንኩ የሚገነባው ሁለገብ ህንጻ በአሁኑ ወቅት የንግድና ኢንቨስትመንት ማዕከልነቱ እየጨመረ ለመጣው የወላይታ ሶዶ ከተማ ትልቅ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ተገልጸዋል፡፡
ባንኩ በስፍራው ደረጃውን የጠበቀ ህንጻ በመገንባት ለከተማዋ ውበትና መልካም ገጽታ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት አሻራውን እንደሚያኖርም ተገልጸዋል፡፡


Demos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up