ብርሃን ባንክ ለገበታ ለሃገር ፕሮክቶች ማስፈፀሚያ የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ብርሃን ባንክ አ.ማ ለሶስት ሃገራዊ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የሚያግዝ የ 20 ሚሊየን ብር ድጋፍ “ለገበታ ለሀገር”; ማድረጉን አስታወቀ፡፡ ባንኩ ይህን የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ያስታወቀው መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም የባንኩ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች በተገኙበት በተከናወነ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

የብርሃን ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም አላሮ መንግስት ሃገራዊ ፋይዳቸው የጎሉ በርካታ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ እንደሆነ አስታውሰው ለዚህም ማሳያ የሚሆኑት ከጥቂት ጊዜያት በፊት ባንካችን የበኩሉን ድጋፍ ያበረከተበት የሸገር ፓርክን ጨምሮ ለመዲናችን ተጨማሪ ውበትን ያላበሰው የወንድማማችነት ፖርክ ይገኙበታል ብለዋል፡፡ መንግስት በሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክቶች አስጀምሮ በአጭር ጊዜ አሳክቶ ያሳየንን እና አዋጭነታቸው የተመሰከረላቸው የቱሪዝም ተኮር ፕሮጀክቶች አድማስ በማስፋት በጎርጎራ፣ በኮይሻ እና በወንጪ ሊያሳካ የወጠናቸውን ግዙፍ ፕሮጀክቶች ባንኩ እንደሚደግፈው አስታውቀዋል  ፕሬዚዳንቱ ባንኩ ለእነዚህ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ ያግዝ ዘንድ የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሲያደርግ ፕሮጀክቶቹ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት ሲሆኑ የሃገራችንን  የቱሪዝም መዳረሻ  አማራጮችን ከማስፋት ጎን ለጎን የውጭ ምንዛሪ አቅሟን ለማሳደግ አስተዋፅኦ እንደሚደርግልን ፅኑ እምነት እንዳላቸው ኘሬዝደንቱ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩልም ባለፉት ሁለት የትምህርት ዘመናት ለከተማ መስተዳድሩ እንዲሁም በችግር ላይ ለሚገኙ እና በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ስር እየተረዱ ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ ተማሪዎች በርካታ የትምህርት ቁሳቁሶችን እና የገንዘብ ድጋፍ ባንኩ መለገሱን ያስታወሱት የባንኩ ፕሬዚዳንት፣ ለ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ስር ለሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለሟሟላት እና ለተማሪዎች ምገባ የሚረዳ የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ መለገሱን አቶ አብርሃም  አስታውቀዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር የአዳዲስ የብር ኖቶች ወደ ገበያ መግባትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የነባሮቹን የብር ኖቶች በአዳዲሶቹ የመቀየር ስራን በስፋት በማከናወን ላይ እንደሚገኝም የባንኩ ፕሬዚዳንት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ አንስተዋል፡፡ ባንኩ በመላው ሃገሪቱ በሚገኙ በ238 ቅርንጫፎቹ የገንዘብ ለውጡን እሁድ ጨምሮ እያከናወነ  እንደሚገኝ እና እስከ አሁን ድረስ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የብር 1.4 ቢሊየን አዳዲስ የገንዘብ ኖቶችን ተረክቦ ብር 1.1 ቢሊየን የሚሆነውን መቀየር መቻሉን ገልፃል፡፡  በተጨማሪም የአዲሱ የገንዘብ ኖት ለውጥ ከተጀመረ ወዲህ 22,871 አዳዲስ የባንክ ሂሳቦች የተከፈቱ ሲሆን በነዚህም  ሂሳቦች ብር 586 ሚሊዮን የተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል፡፡

መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም

አዲስ አበባ

እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!!Demos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up