ብርሃን ባንክ የሎተሪ ዕጣ አወጣጥ ስነስርዓቱን አከናወነ

ብርሃን ባንክ የ‹‹ይቆጥቡ ይሸለሙ እና ይመንዝሩ ይቀበሉ›› የሎተሪ ዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት አከናወነ፡፡ ባንኩ 1ኛ ዙር ይቆጥቡ ይሸለሙ እና 3ኛ ዙር የውጭ ምንዛሬ ግኝት ማበረታቻ የሽልማት ዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱን በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ አከናውኗል፡፡

ባንኩ ከመጋቢት 8/2013ዓ.ም እስከ መስከረም 3/2014ዓ.ም ድረስ በሃገር ውስጥ ቁጠባና በውጭ ምንዛሬ ላይ ያተኮሩ መርሃግብሮችን ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሶ፤ በዛሬው ዕለት በብሄራዊ ሎተሪ በተከናወነ የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት ላይ ሽልማት የሚያስገኙ ዕጣዎች በይፋ ለባለ ዕድለኞች መውጣታቸውን አስታውቋል፡፡

በይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃግብሩ ደንበኞች ከ200 ብር ጀምሮ በመቆጠብ በአቅራቢያቸው በሚገኝ ቅርንጫፍ ሲቆጥቡ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ፤ የቁጠባ ባህላቸውን ከማሳደግ ጎን ለጎን በሽልማት መርሃግብሩ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ሲያበረታታ ቆይቷል፡፡ በዚህም የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ዘመናዊ የቤት መኪናና ባለሶስትእግር ተሸከርካሪዎችን ጨምሮ በርካታ አጓጊ ሽልማቶች የተካተቱበት መሆኑ ታውቋል፡፡

የውጪ ምንዛሬ ማበረታቻ ሽልማት የሚያስገኙ ዕጣዎች የሎተሪ ዘርፍ በበኩሉ ደንበኞች የውጭ ሃገራት ገንዘቦችን በባንኩ ቅርንጫፎች በኩል በመመንዘር እንዲሁም ከወዳጅ ዘመድ የተላኩላቸውን የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦች ከባንኩ ቅርንጫፎች እንዲቀበሉ ቀልጣፋ ስርዓትን በመዘርጋት ደንበኞች ህጋዊ የባንክ ስርዓትን በመጠቀም ለሃገር ኢኮኖሚ እድገት የበኩላቸውን እንዲበረክቱ ለማስቻል በማሰብ የተዘጋጀ መሆኑን ባንኩ ገልጸዋል፡፡ በዚህም ዘርፍ ባንኩ ተጨማሪ ዘመናዊ የቤት መኪና፤ ባለ ሶስትእግር ተሸከርካሪዎችን ጨምሮ በርካታ አጓጊ ሽልማቶች ያካተተ መርሃግብር ተግብሮ ይህንኑ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት አከናውኗል፡፡

ባንኩ በዕጣ ማውጣት ስነስርዓቱ ወቅት ለባለዕድለኞች የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

የዕድለኛ ቁጥሮችን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን  lotto_winning_numbers ይጫኑ!Demos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up