ብርሃን ባንክ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዢ ፈፀመ፡፡

ብርሃን ባንክ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዢ ፈፀመ፡፡

ብርሃን ባንክ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማፋጠን የሚረዳ የብር 5 ሚሊዩን የቦንድ ግዢ ፈፀመ፡፡ ባንኩ ይህን ያስታወቀው መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በባንኩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ  በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም አላሮ በመግለጫው ላይ እንዳስታወቁት ሃገራችን ኢትዮጵያ በርካታ የውሃ አቅም ያላት መሆኑን አስታውሰው ይህ ዓቅም እያደገ ለመጣው የሃይል አቅርቦት አይነተኛ መፍትሄ ያለው መሆኑን በመረዳት ባለፉት ሁለት አስርታት የተለያዩ የሃይል ማመንጫዎችን በመገንባቷ በርካታ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎችን እውን ልታደርግ ችላለች ብለዋል፡፡ የዛሬ 10 ዓመት ደግሞ ለአመታት እንደ ሃገር ያልተሞከረውን እና በውጥን ደረጃ የነበረውን ብሔራዊ መገለጫችን የሆነውን ታላቁን የአባይ ወንዝ በራስ አቅም በመገንባት ሃገራችን ያለባትን የሃይል አቅርቦት ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ለመፍታት በማለም ግንባታውን በመጀመሯ ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ በተለያየ መልኩ ድጋፋችንን አሳይተናል ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አክለውም የመሰረት  ድንጋዩ ከተጣለበት የዛሬ 10 ዓመት ጀምሮ ግንባታውን ጨምሮ በርካታ ሂደቶችን ማለፉን አስታውሰው ብርሃን ባንክ ለዚህ ታላቅ ብሄራዊ ዓርማ ለሆነው ግድባችን መገንቢያ ይሆን ዘንድ በወቅቱ በገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡

የባንኩ ኘሬዝደንት ታለቁ የህዳሴ ግድባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ የግንባታ ስራው እየተፋጠነ እና ወደ ማገባደጃው ምዕራፍ መድረሱ የባንካችን የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የባንኩ የማኔጀመንት አካላት እንዲሁም መላው የባንኩ ማህበረሰብ በከፍተኛ አድናቆት እንደሚመለከተው ገልፀዋል፤ የህዳሴ ግድባችን ሲጠናቀቅ በሃገር ውስጥ ያለውን የሃይል እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ከመቅረፉም አልፎ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ረገድ ለሃገራችን ከፍተኛ አዎንታዊ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳን የሚያመጣ ታላቅ አሻራችን በመሆኑ ባንካችን ለግድባችን የበኩሉን በማበርከቱ ከፍተኛ ኩራት ይሰማዋል ብለዋል፡፡

አቶ አብርሃም አክለውም ብርሃን ባንክ ከዚህ ቀደም ለገበታ ለሀገር፤ ገበታ ለሸገር፤ ለአዲስ አበባ ከተማ የተማሪዎች ምገባ እና የትምህርት ቁሳቁስ ማሟያ፣ የኮሮና ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ፣ ለኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ማዕከል፣ እንዲሁም በሌሎች በርካታ አገራዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉንም  አስታውሰው ለወደፊቱም ባንኩ እንደ ኮርፖሬት ዜጋ በአገራዊ ልማት እና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚደረገውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ላረጋግጥ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ 0116507707Demos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up