ለብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮኖች በሙሉ እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ ስለመስጠት

ለብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮኖች በሙሉ እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ ስለመስጠት

የብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. በ2010 ዓ.ም. በሚያካሄደው የባለአክስዮኖች 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከሚቀርቡ አጀንዳዎች መካከል አንዱ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ምርጫ ማከናወን ነው፡፡ ይህ ምርጫ የሚከናወነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣዉ መመሪያ ቁጥር SBB/63/2015 እና የባንኩ ባለአክስዮኖች 7ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ባጸደቀው  “የብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. የአስመራጭ ኮሚቴ እና የዳይሬክተሮች ቦርድ የጥቆማ እና የምርጫ አፈጻጸም መመሪያ” መሰረት ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ጥቅምት 26 ቀን 2009 ዓ.ም. የተካሔደው የባንኩ 7ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የአስመራጭ ኮሚቴ ማቋቋሙ ይታወሳል፡፡

የተቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን ሲያከናውን ቆይቶ ጥቆማዎች ለመቀበል ተዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም የባንኩ ባለአክስዮኖች ለባንኩ ሁለንተናዊ እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ይችላሉ ብለው የሚያምኑባቸውን ብቁ እጩዎችን ከግንቦት 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ እንዲጦቁሙ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

ተጠቋሚ እጩዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርት፡

 1. ዜግነታቸው ኢትዮጲያዊ መሆን አለበት፡፡
 2. እድሜያቸው  ቢያንስ 30 ዓመት መሆን አለበት፡፡
 3. የብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮን መሆን አለባቸው፡፡
 4. እጩ ተጠቋሚዎቹ ቢመረጡ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ለመሥራት ፈቃደኛ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ቢያንስ 1/4ኛ የሚሆኑ የቦርድ አባላት አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ  ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ሊኖራቸው ሲገባ ቀሪዎቹ 3/4ኛ የቦርድ አባላት ቢያንስ የመጀመሪያ ድግሪ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
 6. እጩ ተጠቋሚዎቹ በቢዝነስ ማኔጅመንት፤ በባንክ ሥራ፤ በፋይናንስ፤ በአካውንቲንግ፤ በሕግ፤ በኦዲቲንግ፤ በኢኮኖሚክስ፤ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፤ በኢንቨስትመንት ማኔጅመንት፤  የትምህርት መስክ የተመረቁና የጾታ ስብጥራቸውም ተመጣጣኝ ቢሆን ይመረጣል፡፡
 7. በብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ዉስጥ በቦርድ አባልነት ለስድስት ተከታታይ ዓመታት (ለሁለት የሥራ ዘመን/ተርም/) በቦርድ አባልነት አገልግለው ከቦርድ አባልነት ከለቀቁ ስድስት ዓመት የሞላቸው መሆን አለበት፡፡
 8. የባንኩ አስመራጭ ኮሚቴ አባል ለዳይሬክተሮች ቦርድ እጩ ተመራጭ መሆን አይችልም፡፡
 9. በቦርድ አባልነት ከተመረጡ ከባንክ ሥራ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሥልጠናዎች ለመውሰድ ፈቃደኛ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 10. መልካም ስነምግባርና ማህበራዊ ተቀባይነት ያላቸውና፤ በወንጀል ተከሰው ያልተቀጡና ወይም ጥፋተኛ ያልተባሉ መሆን ይኖባቸዋል፡፡
 11. ተጠቋሚው ድርጅት ከሆነ ድርጅቱን ወክሎ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ለመሆን የሚወዳደረው የተፈጥሮ ሰው ማንነትና የትምህርት ደረጃ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ ሊጠቀሱ ይገባል፡፡
 12. ተጠቋሚው የብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክም ሆነ የሌሎች ባንኮች ተቀጣሪ ሠራተኛ መሆን የሌለባቸው ሲሆን፣ በጥቆማው ወቅት በሌሎች ባንኮችም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆነው እየሠሩ መሆን የለበትም፡፡
 13. ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች መጠቆም የምትፈልጉ ባለአክስዮኖች ለጥቆማ የተዘጋጀውን ቅጽ/ፎርም ከግንቦት 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ በብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቦሌ ድልድይ ወመሳድኮ ሕንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601 ወይንም በባንኩ ቅርንጫፎች በግንባር በመቅረብ ወይም በባንኩ ድህረ ገጽ http://www.berhanbanksc.com ለጥቆማ የተዘጋጀዉን ቅጽ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን አስመራጭ ኮሚቴዉ ያሳዉቃል፡፡

ባለአክሲዮኖች የሞሉትን ቅጽ በብርሃን ኢንተርሽናል ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት ወመሳድኮ ሕንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601  በግንባር በመቅረብ መስጠት ወይም በፓ.ሣ.ቁጥር 14178 አድራሻውን ለብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ በማድረግ ወይም በባንኩ ኢሜል berhanbank1@ethionet.com አያይዘዉ መላክ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-663-2076 እና 0944-724161 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከሐምሌ 30 ቀን 2009 ዓ.ም በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን የማንቀበል መሆኑን ኮሚቴዉ ያሳስባል፡፡

 

የብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ

 

 Leave a Reply

Demos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up