የስብሰባ ጥሪ ለብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖችን 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ኅዳር 30  ቀን 2010 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ  ቦሌ በሚገኘው ሚሊኒየም አዳራሽ  ይካሔዳል፡፡ ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በሙሉ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ኢትዮጲያዊ ዜግነት ያላችሁ መሆኑን የሚያሳይ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ  እንዲሁም በሞባይል አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚላክላችሁን የባለአክስዮን መለያ ቁጥር በመያዝ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪ ያቀርባል፡፡

  1. የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

1.1 የጉባዔውን አጀንዳ ማጽደቅ

1.2 የተከናወኑ የአክሲዮን ዝውውሮችን  ማጽደቅና  አዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል

1.3 የዳይሬክተሮች ቦርድን አመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ

1.4 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥ

1.5 በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን

1.6 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ወርሃዊ አበልና ዓመታዊ ክፍያ መወሰን

1.7 በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን

1.8 የአስመራጭ ኮሚቴ ሪፖርት ማድመጥና  የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ ማካሔድ

1.9 የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ  

                              

  1. የድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

2.1 የጉባዔውን አጀንዳ ማጽደቅ፣

2.2 የማህበሩን መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻል

2.3 የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ

ማሳሰቢያ 

በጉባኤው ላይ ለመገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች  ቀጥሎ በተመለከተው መሠረት በወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  • ጉባኤው ከሚካሄድበት  ቀን  አስቀድሞ  ባሉት  ቀናት ውስጥ ቦሌ ድልድይ  ፊት ለፊት በሚገኘው  የባንኩ  ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የውክልና ፎርም/ቅጽ   በመሙላት  ተወካይ  በመወከል ወይም

  • ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት የተሰጠና በስብሰባው ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት   የሚያስችል ውክልና  ያለው ተወካይ ዋናውን እና  አንድ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ተወካዮች ማንነታችሁን የሚያሳይ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ በጉባኤው እለት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ .ማ.

የዳይሬክተሮች ቦርድLeave a Reply

Demos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up