ብርሃን ባንክ ከፌዴራል  ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ብርሃን ባንክ ከፌዴራል  ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።  የመግባቢያ ስምምነቱ የተፈረመው የባንኩ የኮርፖሬት ፕላኒንግ እና ስትራቴጂ ማኔጅመንት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰሎሞን አሰፋ እና የፌዴራል ስነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነሃሴ 24 ቀን/2013 ዓም በስካይ ላይት ሆቴል በተደረገ ስነስርዓት ላይ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት Digital Ethiopia 2025 የተባለ የዲጂታል ስትራቴጅ ቀርፆ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህን ስትራቴጂ ለማሳካት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የመንግስትና የግል ተቋማትም ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ በትስስር መስራትን ይጠይቃል፡፡ ይህንኑ ባማከለ መልኩ በፌደራል የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ እና በብርሃን ባንክ መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ የዚሁ ጥረት አካል ሆኗል።  የመግባቢያ ሰነዱ መፈረም ባንኩ ከመስከረም 2012 በኋላ የተመዘገቡ የውክልና ሰነዶችን ኦንላይን እንዲያረጋግጥ የሚያስችለው ሲሆን ይህም ከአሁን በፊት የነበረውን የውክልና ሰነዶችን ወደ ፌደራል የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ በመላክ ይደረግ የነበረውን የማረጋገጥ ሥራ የሚያስቀር ነው፡፡

በዚህም መሰረት ይህ የመግባቢያ ስምምነት መፈረም፦

  1. ደንበኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት ማግኘት ያስችላቸዋል
  2. የማጭበርበር እና ሌሎች ህገ፟ወጥ ድርጊቶችን መከላከል ያስችላል፡፡ በዚህም በገንዘብ እንዲሁም የባንኮችን ስም በማጉደፍ ከሚደርስ ጉዳት መከላከል ያስችላል
  3. የባንክ ሠራተኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር የውክልና ሰነዶችን ትክክለኛነት ለማረጋግጥ ከሚጠፋ የጊዜ፣ ገንዘብና የሰው ሃይል መባከን ይታደጋል
  4. የውክልና ሰነዶችን ትክክለኛነት ለማረጋግጥ በሚላከው ሰው ታማኝነት ላይ ብቻ የተመሰረተውን ዘዴ በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች በቀላሉ ኦንላይን ማረጋገጥ ያስችላል
  5. የፌደራል የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲም የውክልና ሰነዶችን ለማረጋገጥ የነበረበትን ጫና ያስቀራል ተብሏል።


Demos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up