ብርሃን ባንክ ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በርካታ የትምህርት ቁሳቁሶችን አበረከተ

ብርሃን ባንክ ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በርካታ የትምህርት ቁሳቁሶችን አበረከተ

ብርሃን ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አነሳሽነት በተጀመረው ‘ስጦታ ለአዲስ አበባዬ’ የበጎ አድራጎት ንቅናቄ መሰረት በመስተዳድሩ በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን  ለሚከታተሉ የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለማሟላት በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ማህበራዊ ሃላፊነት ለመወጣት በማሰብ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ደብተሮች እና እስክሪብቶዎች ሐምሌ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት በመገኘት ለከተማ መስተዳድሩ አበርክቷል፡፡ ከባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም ከባንኩ ፕሬዚዳንት በኩል በባንኩ በስጦታ የተበረከቱትን ባለ 50 ቅጠል 350,000 የመማሪያ ደብተሮችን እና 150,000 እስክሪብቶዎች የተቀበሉት የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ብርሃን ባንክ ለሃገር ተረካቢ ተማሪዎች ላደረገው ተምሳሌታዊ የሆነ ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበው ሌሎች ተቋማትም መሰል ድጋፎችን እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ ስጦታዎቹን ለክቡር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ባስረከቡበት ወቅት የባንኩ የዳይሬክሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጉማቸው ኩሴ እንደገለፁት ብርሃን ባንክ ለትርፍ የተቋቋመ ተቋም ቢሆንም ተቀዳሚ ተልዕኮው ግን ለማህብረሰቡ በተለይም እንዲህ በመሳሰሉ እና ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ጉዳዮች ላይ በግንባር ቀደምነት በመገኘት የበኩሉን ጉልህ አሻራ ማሳረፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዚህ ‘ስጦታ ለአዲስ አበባዬ’ በተሰኘው መልካም አላማን አንግቦ ለተነሳው ግብ መሳካት ብርሃን ባንክ የበኩሉን ለመወጣት ካለው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ የተበረከተው የደብተር እና የእስክሪብቶ ስጦታ በገንዘብ ሲተመን 5 ሚሊዮን ብር የሚደርስ መሆኑን የገለፁት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አብሃርም አላሮ ከዚህ ቀደምም ለ2011 ዓም የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት ሙዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት እና ሜሪ ጆይ የህፃናት እና የአረጋውያን ማዕከል ለሚደገፉ ሕፃናትም በርካታ የትምህርት ቁሳቁሶችን ማበርከቱን አስታውሰዋል፡፡ በሌላም በኩል የባንኩ ኘሬዝደንት ባንኩ የማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለተፈናቀሉ እና በድንገተኛ አደጋ ለተጐዱ እንዲሁም በፌደራል እና በክልል መንግሥት ደረጃ ለታቀዱ የዕድገት እና የልማት ኘሬጀክቶች በከፍተኛ ደረጃ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀው ባንኩ ይህንን መሰል ተግባር ለወደፊቱም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡Demos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up