ብርሃን ባንክ የሎተሪ ዕጣ ሽልማትን ለባለዕድለኞች አስረከበ

ብርሃን ባንክ የ3ኛ ዙር የ‹ይመንዝሩ ይቀበሉ› እና 1ኛ ዙር የ‹ይቆጥቡ ይሸለሙ› ማበረታቻ ሽልማትን ለባለዕድለኞች አስረከበ፡፡

ባንኩ በመርሃግብሩ 2 ዘመናዊ ሱዙኪ የቤት መኪና፤ 4 ባለሶስትእግር ተሽከርካሪዎችና 10 ቴሌቪዥኖችን ጨምሮ በርካታ አጓጊ ሽልማቶችን የባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራሮች፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ባለዕድለኞች በተገኙበት በደማቅ ስነስርዓት አስረክቧል፡፡

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ለባለዕድለኞች የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባንኩ ተ/ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ቤተልሄም ጌታቸው፤ ቁጠባን ለማበረታታት ለመጀመሪያ ጊዜ የይቆጥቡ ይሸለሙ የሎተሪ ፕሮግራም መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም ደንበኞች ከውጭ የሚላክላቸውን የውጭ ሃገራት ገንዘቦች በህጋዊ መንገድ ብቻ እንዲመነዘር ለማድረግ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ባንኩ በ‹ይመንዝሩ ይቀበሉ› እና በ‹ይቆጥቡ ይሸለሙ› መርሃግብሩ የሎተሪ ዕጣ አወጣጥ ስነስርዓትን በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ ማከናወኑ ይታወሳል፡፡

የኢቲቪን የዜና ሽፋን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን  https://www.youtube.com/watch?v=TesnUInIhmo

ይጫኑDemos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up