ብርሃን ባንክ እ.ኤ.አ በ2019/20 ዕድገቱን ያስቀጠለበትን ውጤት አስመዝገበ

ብርሃን ባንክ

ጋዜጣዊ መግለጫ

ብርሃን ባንክ እ.ኤ.አ በ2019/20 ዕድገቱን ያስቀጠለበትን ውጤት አስመዝገበ

ብርሃን ባንክ 11ኛ መደበኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ጎልፍ ክለብ ቅጥር ግቢ አካሂዷል። በጉባኤው ላይ የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጉማቸው ኩሴ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2020 የተጠናቀቀውን የባንኩን ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለባለአክሲዮኖች አቅርበዋል። በቀረበው ሪፖርት መሰረት በበጀት ዓመቱ በሃገራችን የታየው የፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የህብረተሰብ ጤና ተያያዥ እና ማህበራዊ ተግዳሮቶች ከፍተኛ የነበሩ ቢሆንም ባንኩ የተገኙ እድሎችን በአግባቡ ለመጠቀም እና ተግዳሮቶችን ለመሻገር የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ቀይሶ ተግባራዊ በማድረጉ በሁሉም የስራ ዘርፎች አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉ ተገልጿል።

በቀረበው ሪፖርት መሰረት ባንኩ ከትርፍ ግብር በፊት ብር 707.5 ሚሊዮን አጠቃላይ ትርፍ ማስመዝገበ የቻለ ሲሆን ይህም አፈጻጸም ካለፈው የበጀት ዓመት ጋር በንጽጽር ሲታይ የ ብር 127.4 ሚሊዮን ወይንም የ 22 በመቶ እድገት አሳይቷል። በመሆኑም የባንኩ ብር 1000 ዋጋ ያለው አክሲዮን የትርፍ መጠኑ ብር 259 የደረሰ ሲሆን ይህም ባንኩ ባለፈው የበጀት ዓመት ካስመዘገበው አፈጻጸም ጋር ሲወዳደር የተሻለ ሆኗል።

ሃብትን በማሰባሰብ ረገድ በበጀት ዓመቱ የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 16.6 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ካለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ ብር 1.6 ቢሊዮን ወይንም የ11.0 በመቶ እድገት ማስመዝገብ ችሏል። በተመሳሳይም በበጀት ዓመቱ ባንኩ 155.7 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ መሰብሰብ ችሏል። የባንኩ የብድር ክምችት ደግሞ ባለፈው በጀት ዓመት ከነበረው ከብር 10.2 ቢሊዮን በብር 2.5 ቢሊዮን ወይንም በ24.5 በመቶ በማደግ ብር 12.7 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን የባንኩ አጠቃላይ ሃብት ደግሞ ከአለፈው ዓመት በ11.4 በመቶ እድገት በማስመዝገብ ብር 21.4 ቢሊዮን ደርሷል፡፡  እንዲሁም የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል ከአለፈው ዓመት በ22.5 በመቶ በማደግ ብር 3.4 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን  የተከፈለ ካፒታል ደግሞ የ 22.6 በመቶ እድገት በማሳየት ብር 2.45 ቢሊዮን ደርሷል፡፡ ይህም ብርሃን ባንክ በበጀት ዓመቱ በሁሉም የአፈጻጸም ዘርፎች አበረታች ውጤት ማስመዝገቡን በተጨባጭ ያሳያል።

ባንኩ በበጀት ዓመቱ ውስጥ 31 አዳዲስ ቅርንጫፎችን የከፈተ ሲሆን አጠቃላይ የቅርንጫፍ ስርጭቱን 231 ማድረስ ችሏል። የባንኩ የደምበኞች ቁጥር ደግሞ በ 132 ሺህ ወይም በ 20.1 በመቶ በማደግ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 789 ሺህ በላይ መድረስ ችሏል። በተጨማሪም በባንኩ በኩል የትምህርት ቤቶች ክፍያ መፈጸም የሚያስችል ‘‘ስኩል ፔይ’’ የተባለ አዲስ ዓይነት የባንክ አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ ላይ እንዲውል ያደረገ ሲሆን የበረራ ትኬቶችን ዲጂታላይዝድ በማድረግ በቀላሉ ትኬት መቁረጥ የሚያስችል ‘‘ጉዞ ጎ’’ የተባለ የባንክ አገልግሎትም ሥራ ላይ ማዋል ተችሏል። ከዚህም በላይ ባንኩ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያልውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የቪዛ እና የማስተር ካርድ አገልግሎቶችን መስጠት ጀምሯል፡፡

በሌላ በኩል በከተማችን የፋይናንስ ማዕከል ተብሎ በተለየው አካባቢ ባንኩ ለዋና መሥሪያ ቤት ጊዜያዊ ህንፃ ግንባታ የሚሆን 2,295 ካሬ ሜትር መሬት ግዥ መፈጸሙን ከዋና ዋና የባንኩ የበጀት ዓመቱ ስኬቶች መካከል የሚጠቀስ መሆኑን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው ያሳወቁ ሲሆን ባንኩ ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ለዋናው መሥሪያ ቤት ግንባታ ያቀረበውን የመሬት ጥያቄ በመከታተል ላይ እንደሚገኝም አሳውቀዋል። በተጨማሪም ባንኩ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ ብር 30 ሚሊዮን ለተለያዩ ሃገራዊና ልዩ ልዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ድጋፍ አድርጓል፡፡

በመጨረሻም ባንኩ በቀጣይ ዓመታት አሁን ያስመዘገበውን ውጤት ለማስቀጠል የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ እንደሚንቀሳቀስ የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አስታውቀዋል።

 

BERHAN BANK

PRESS RELEASE

Berhan Bank Recorded Notable Profit Growth in 2019/20 F.Y.

Berhan Bank conducted the 11th Ordinary Annual General Meeting of Shareholders on Tuesday, December 22, 2020 at the Golf Club compound, Addis Ababa.

Ato Gumachew Kussie, Chairman of the Board of Directors, presented the Bank’s Annual Performance Report, which was closed on June 30, 2020, to the shareholders. He mentioned, despite the political, economic, health related and social challenges persisted in the country during the reporting period, the Bank has achieved notable results in all key performance indicators and it realize the result by designing workable business strategies to tap the available business opportunities and properly addressing the prevailing challenges.

According to the report, the Bank posted a record high profit before tax of Birr 707.5 million during 2019/20 fiscal year. It was further revealed that the profit registered exhibited an annual increment of Birr 127.4 million or 22.0 percent compared with the Bank’s preceding year’s performance. With this, the Bank’s basic Return on Equity (RoE) reached 25.9 percent.

In terms of resources mobilization, the report indicated that the Bank’s deposit surged to Birr 16.6 billion, exhibiting an annual increment of Birr 1.6 billion or 11.0 percent. Likewise, the annual foreign exchange inflow reached USD 155.7 million. Furthermore, the Bank’s outstanding loans and advances grew to Birr 12.7 billion from its level of 10.2 billion in the preceding fiscal year, registering a net annual increment of Birr 2.5 billion or 24.5 percent. The Bank’s total assets reached Birr 21.4 billion, exhibiting Birr 2.2 billion or 11.4 percent growth over the preceding year. The paid up and total capital reached Birr 2.45 and Birr 3.4 billion respectively, depicting a respective growth of 22.6 percent and 22.5 percent respectively.

With regards to branch expansion, it was reported that the Bank opened 31 new branches during the captioned period. As a result, the total branch network of the Bank reached 231 at the close of the reporting period. Likewise, the number of the Bank’s account holders surged by 132 thousand or 20.1 percent and have reached above 789 thousand. Regarding digital financial services, the Bank managed to launch School Pay service developing a fully integrated school fee management system; digital flight ticket booking service named as GuzoGo and commenced VISA and MasterCard service which are believed to enhance the market competitiveness of the Bank in the industry.

As another success story, the chairperson has announced the purchase of a land of 2,295 m2 near the future financial center of the city to build transitional head quarter of Berhan Bank and also the Bank’s request for plot of land to build the Bank’s head quarter is under process with Addis Ababa City Administration Office. On the other hand, the Bank has donated nearly Birr 30 million for national and societal related initiatives to demonstrate its social responsibility.

Finally, the chairman cited that, the Bank has drawn effective strategies to sustain the growth momentum and register greater achievements in the years to come.

 

 Demos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up