ብርሃን ባንክ የትምህርት ቤቶች ክፍያዎችን መከወኛ (Berhan School Pay) አዲስ ስርዓት ተግባራዊ ማድረጉን አስታወቀ

ብርሃን ባንክ አ.ማ ለትምህርት ቤቶች ክፍያዎችን በኤሌክትሮኒክ ስርዓት አማካኝነት ማከናወን የሚችሉበትን “Berhan School Pay”  የተሠኘ አዲስ የክፍያ አገልግሎት ወደ ተግባር ማስገባቱን አስታወቀ፡፡ ይህንን በዓይነቱ ልዮ የሆነውን የክፍያ ስርዓት ጳጉሜን 3 ቀን 2012 ዓ.ም የባንኩ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት በተገኙበት በይፋ ያስጀመሩት የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ናቸው፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የባንኩ ኘሬዚደንት አቶ አብርሃም አላሮ እንደገለፁት ባንኩ ይህንን ዘመናዊ የክፍያ ስርዓት ለመተግበር በጥናት ላይ የተደግፈ ሰፊ ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበር እና በዛሬው ዕለትም በይፋ መጀመሩ ለባንኩ ደምበኞች የአገልግሎት ዕርካታ ከመጨመር ባሻገር መንግስት በአገር አቀፍ ደረጃ ወደ ዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ለመግባት በሚያደርገው ዘርፈ ብዙ ጥረት የራሱን ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ይህ የክፍያ ስርዓት ይፋ ከመደረጉ በፊት በተለያዩ ጊዜያት በባለድርሻ አካላት ተገምግሞ ውጤታማነቱ የተረጋገጠ መሆኑን ያስታወቀው ባንኩ፣ የክፍያ ስርዓቱ በትምህርት እና ስልጠና ዘርፍ ያሉ ተገልጋዮችን የገንዘብ መሠብሠብ ሥራ በማዘመን ቀላል፣ ጊዜ ቆጣቢ፣ አመቺ እና አስተማማኝ በሆነ መንገድ እንዲያከናውኑ ከማስቻሉም ጎን ለጎን ክፍያዎቹ እንደተፈጸሙ ክፍያው የተፈፀመለትን ግለሰብ አስፈላጊውን መረጃ ወዲያውኑ (Real Time) በማደራጀት ለየትምህርት ቤቱ  የሚልክ  መሆኑም ተገልጧል፡፡ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቱ የትምህርት ቤት ክፍያ ለሚፈፅሙ የተማሪ ወላጆች ወይም ተማሪዎች እንደከዚህ ቀደሙ በጥሬ ገንዘብ የሚያደርጉትን ክፍያ  በማስቀረት የጉልበት፣ %Demos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up