የባለአክሲዮኖች 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

የብርሃን  ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች  12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ታህሣሥ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጎልፍ ክለብ ይካሔዳል፡፡ ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በሙሉ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም በሞባይል አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚላክላችሁን የባለአክስዮን መለያ ቁጥር በመያዝ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪ ያቀርባል፡፡

የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ

 1. አጀንዳውን ማጽደቅ፤
 2. የተከናወኑ የአክስዮን ዝውውሮችን ማሳወቅና አዳዲስ ባለአክስዮኖችን መቀበል፤
 3. የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ.የ2020/21 ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ ፤
 4. የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ. የ2020/21 ዓመታዊ የሂሳብ ሪፖርት ማዳመጥ ፤
 5. ከዚህ በላይ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 6. በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 7. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ወርኃዊ አበልና ዓመታዊ ክፍያ መወሰን፣
 8. የውጭ ኦዲተሮችን መሰየምና ክፍያቸውን መወሰን፤
 9. የጉባዔውን ቃለጉባዔ ማጽደቅ የሚሉት ናቸው፡፡

ማሳሰቢያ

 • በጉባኤው ላይ የሚገኙ ባለአክሲዮኖች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ /ማስክ/ ማድረግ እና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን መከተል ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • በጉባኤው ላይ ለመገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች  ቀጥሎ በተመለከተው መሠረት በወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

/ጉባኤው ከሚካሄድበት ቀን  አስቀድሞ   ባሉት  ቀናት ውስጥ ቦሌ ድልድይ  ፊት ለፊት በሚገኘው  የባንኩ  ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የውክልና ፎርም/ቅጽ   በመሙላት  ተወካይ  በመወከል ወይም

/በስብሰባው ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ማስረጃ ያለው ተወካይ ዋናውን እና አንድ ፎቶ ኮፒ በጉባኤው እለት ይዞ በመቅረብ

                                                                                ብርሃን  ባንክ .

                                                                               የዳይሬክተሮች ቦርድDemos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up