ብርሃን ባንክ የ2024/25 በጀት ዓመት ዓመታዊ የማኔጅመንት ስብሰባ አካሄደ፡፡

ብርሃን ባንክ ሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ዓመታዊ የስራ አመራር ስብሰባውን በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል፡፡ በስብሰባው ወቅት የባንኩን የ2024/25 በጀት አመት አፈፃፀም ግምገማ የተደረገ ሲሆን የ2025/26 በጀት ዓመት እስትራቴጂክ ዶክመንት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ እንዲሁም በበጀት አመቱ ከፍተኛ አፈፃፀም ላሳዩ ፣ ዲስትሪክት ዳይሬክሮች፤ የመምሪያ ዳይሬክተሮች፤ የክላስተር እና የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች የእዉቅና ሰርተፊኬት እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ስብሰባው የባንኩ ሰራተኞች በበጀት አመቱ ያበረከቱት ውጤት አመርቂ እንደነበር እና ይህን ስኬት ለማስቀጠልና የበለጠ እና ተወዳዳሪ ለመሆን መጠንከር እንደሚያስፈልግ በመግለፅ እንዲሁም ለመጣው ውጤት መላውን ሰራተኛ እና የማኔጅመንት አባላት በማመስገን ተጠናቋል፡፡
Berhan Bank held its annual management meeting on July 18, 2025, to celebrate a successful fiscal year and set the stage for continued growth. The meeting brought together leaders from across the bank to review performance for the 2024/25 fiscal year and outline the strategic plan for the upcoming 2025/26 year.
A major highlight of the event was the recognition of our high-achieving employees. Exceptional district and department directors, cluster managers, and branch managers were awarded certificates and cash prizes for their outstanding performance and dedication.
The gathering concluded with a message of gratitude and encouragement. The bank’s leadership praised all staff and management for their hard work and significant contributions over the past year, expressing confidence that their continued efforts will ensure the bank remains competitive and successful.