ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ፕ/ማ – 02/18
ብርሃን ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለፁትን ሶስት ያገለገሉ አዉቶሞቢሎች ባህርዳር ከተማ ላይ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ. | ለጨረታ የቀረቡ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች | የተመረቱበት ዓ/ም | ብዛት |
1 | ሃይዉንዳይ Grand i10 አዉቶሞቢል | 2014 ዓ/ም | 01 |
2 | ሃይዉንዳይ EON አዉቶሞቢል | 2017 ዓ/ም | 02 |
- ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ሶስት አዉቶሞቢሎች ባህርዳር ከተማ ፓፒረስ ሆቴል ቅጥር ጊቢ ዉስጥ በሚገኘዉ ብርሃን ባንክ የሰሜን ቀጠና ጽ/ቤት በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፣ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ፣ ባህርዳር ከተማ ፓፒረስ ሆቴል ቅጥር ጊቢ ዉስጥ በሚገኘዉ ብርሃን ባንክ የሰሜን ቀጠና ጽ/ቤት፣ ባህርዳር ከተማ በሚገኙ በሁሉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፎች፣ እንዲሁም የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ቦሌ፣ ቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ በመገኘት ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር በተገለፀዉ መሰረት ለሚጫረቱበት ተሸከርካሪ የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ በተናጠል በብርሃን ባንክ ስም የተዘጋጀ C.P.O. ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጠቀሱትን ተሸከርካሪዎች አንድ እና ከዛ በላይ በተናጠል ተወዳድረዉ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ በቀረበዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ በተናጠል በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ C.P.O ጋር አያይዘዉ በታሸገ ኤንቬሎፕ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ/ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ባህርዳር ከተማ ፓፒረስ ሆቴል ቅጥር ጊቢ ዉስጥ በሚገኘዉ ብርሃን ባንክ የሰሜን ቀጠና ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ/ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ባህርዳር ከተማ ፓፒረስ ሆቴል ቅጥር ጊቢ ዉስጥ በሚገኘዉ ብርሃን ባንክ የሰሜን ቀጠና ጽ/ቤትይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል ተሽከርካሪ/ተሽከርካሪዎች ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ላሸነፈበት ተሽከርካሪ/ተሸከርካሪዎች ከስም ማዛወሪያ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን በራሱ ይሸፍናል፡፡
- ጨረታዉ ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን የመሰረዝ መብት አለዉ፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0998422591 / 0920134113 / 0583207417 / 0116631729 ደዉለዉ ማግኘት ይችላሉ፡፡


