ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. “ የስኩል ፔይ ሲስተም ” አሰራርን የበለጠ ለማስተዋወቅ እና ለመሸጥ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ጥሪ የተደረገላቸው 50 ተጋባዥ እንግዶች የተገኙ ሲሆን የግል ትምህርት ቤት ባለቤቶች ፣ የከፍተኛ የትምህርት ተቋም ባለቤቶች እና ተወካዮች ፣ የባህር ዳር ከተማ የግል ትምህርት ማህበር ፕሬዘዳንት ፣ በተገኙበት በዩኒሰን ሆቴል ገለጻው ተከናውኗል።
የባንኩ ተ/ም/ፕ/ ኦፕሬሽን አቶ ሚሊዮን ዘለቀ ፣ ማርኬቲንግ እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግሩም ታሪኩ ፣ ዲጂታል ፋይናንሲንግ ሰርቪስ ዳይሬክተር አቶ ፈዬራ ኢጀታ ፣ የሰሜን ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ጌታነህ በተገኙበት የእንኳን ደህና መጣችሁ መክፈቻ ንግግር በተ/ም/ፕ የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም የዲጂታል ፋይናንስ ዳይሬክተር ስለ ሲስተሙ ሰፊ ገለጻ ሰጥተዋል። በመቀጠልም ከተጋባዥ እንግዶች ጋር ስለ ስኩል ፔይ መተግበሪያ ሲስተም ያላቸውን ጥያቄ በማንሳት ሰፊና ውይይት የተካሄደ ሲሆን በተለይም ሲስተሙ ከሌሎች ተመሳሳይ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪነቱን ለማስቀጠል እንዲችል እና ተጠቃሚዎች እንዲመርጡት ተማሪዎች የሚፍልጓቸውን መፅሃፍት የሚያገኙበት ሲስተም ላይብረሪ እና የት/ቤት ባለቤቶችን አስተማሪዎችን እና ተማሪዎችን የሚያገኛኝ ኢ-ለርኒንግ የተሰኘ አቅርቦቶችን ያካተተ እንዲሆን አበክረው ጠይቀዋል፡፡
በመጨረሻም ቀደም ብለው ሲስተሙን መጠቀም ለጀመሩ 3 ትምህርት ቤቶች የእውቅና ሰርተፊኬት የተሰጠ ሲሆን የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር ፕሬዘዳንት ይሄንን ሲስተም ከሌሎች ባንኮች ቀደም ብሎ ወደ ክልሉ የመጣ መሆኑን በመግለጽ ባንኩን አመስግነው እንደ ባህር ዳር ካሉ ሰፋፊ ከተሞች ጋር መስራት የትምህርት ሲስተሙን በማሻሻል እና መምህራንም ከክፍያ መቆጣጠር ወጥተው የትምህርት ሂደቱ ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ እንደሚያግዝ በመጥቀስ ይሄንን ሲስተም ሁሉም የትምህርት ተቋማት መጠቀም ቢጀምሩ ጠቀሜታው ከፍ ያለ እንደሚሆን በማረጋገጥ ተናግረዋል። እንዲሁም ሲስተም ላይ የተመረኮዘ አሰራርን በመጠቀም ቀዳሚ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል። የትምህርት ቤት ባለቤቶችም እና ስራ አስኪያጆች የትምህርት ዘርፉ ላይ ትኩረት በመስጠት ይሄን አይነት ጠቃሚ ስራ በመሰራቱ ምስጋና አቅርበዋል።
በመጨረሻም የትውውቅ እና የምሳ ፕሮግራም ተካሂዷል።