ብርሃን ባንክ የ2025/26 በጀት ዓመት አፈጻጸም፣ በላቀ ውጤት እና ስኬታማ አፈጻጸም አጠናቀቀ!!

ባንኩ ከግብር በፊት 5.06 ቢሊዮን ብር ትርፍ በማስመዝገብ የፋይናንስ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ ያሳደገ ሲሆን፣ ይህ አፈጻጸም ከባለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር 76.9 በመቶ ብልጫ አለው። በተመሳሳይ መልኩ አጠቃላይ ገቢውም ወደ 12.37 ቢሊዮን ብር በማደግ የ46.6 በመቶ ጭማሪ አስመዝግቧል።

በሌላ በኩል፣ በደንበኞች እምነት የታጀበው የተቀማጭ ገንዘብ ክምች በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን ባለፈው አመት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር 25.6 % ብልጫ የደረሰ ሲሆን፣ የተከፈለ ካፒታልም ወደ 6.33 (47.5%) ቢሊዮን ብር በማደግ የባንኩን የውስጥ አቅም በእጅጉ አጠናክሮታል።
ከዚህም ባሻገር፣ በበጀት ዓመቱ 407.18 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ለሀገር ኢኮኖሚ የሚጠበቅበትን ድርሻ በተሳካ ሁኔታ ተወጥቷል።
በበጀት ዓመቱ በስራ አፈፃፀም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ መምሪያዎች:ዲስትሪክቶች : ቅርንጫፎች እና ሰራተኞች የገንዘብ ሽልማት እና የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቷል።
ዕውቅና ለተሰጣችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን።

ብርሃን ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!