ማሳሰቢያ

የብርሃን ባንክ ተወካይ በመምሰልና ወደ ደንበኞች በመደወል የኦቲፒ (OTP) ሚስጥር ቁጥር የሚጠይቁ እና ያለፈቃድ የገንዘብ ዝውውር ለማድረግ የሚሞክሩ አጭበርባሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አስተውለናል።

ስለሆነም ውድ ደንበኛችን፦
👉 ባንካችን የኦቲፒ (OTP) ቁጥር በስልክ፣ በፅሁፍ መልዕክት (SMS)]፣ በኢሜይል ወይም በማንኛውም ሌላ የመገናኛ መስመር በፍጹም የማይጠይቅ መሆኑን ተገንዝበው ፤ የኦቲፒ ቁጥርዎን ለማንም ሰው ወይም አካል አሳልፈው እንዳይሰጡ እናሳስባለን።

እንዲህ ዓይነት የማጭበርበር ሙከራዎች ሲያጋጥምዎ፣ ወዲያውኑ ግንኙነቱን በማቋረጥ ጉዳዩን በይፋዊ የደንበኞች አገልግሎት መስመራችን 8292 አማካኝነት ለባንኩ በአስቸኳይ ሪፖርት ያድርጉ።

ብርሃን ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!