በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣367(1) እና 370 እንዲሁም በአክስዮን ማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ 17(1) እና 18(1) መሰረት የብርሃን ባንክ አክስዮን ማህበር የባለአክስዮኖች 7ኛ አስቸኳይና 17ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 15 ቀን 2019 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ አዲስ አበባ ከተማ፤ ሲኤምሲ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሔዳል፡፡
በመሆኑም የተከበራችሁ ባለአክስዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙልን የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
1. ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
1.1 የአክስዮን ማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት አድራሻ
አዲስ አበባ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የቤት
ቁጥር 2185፤ ድረ-ገጽ www.berhanbanksc.com
1.2 የአክስዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር = 06/1/28428/01
1.3 የአክስዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና
ገንዘብ/ካፒታል/= 6,328,419,000.00
1.4 የአክስዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና
ገንዘብ/ካፒታል/= 6,328,419,000.00
2. የ7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
2.1 አጀንዳውን ማጽደቅ
2.2 የባንኩን/ማህበሩን/ ካፒታል ማሳደግ
2.3 የባንኩን/ማህበሩን/ መመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻል
3. የ17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
3.1 አጀንዳውን ማጽደቅ፤
3.2 የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ
3.3 የተከናወኑ የአክስዮን ዝውውሮችን ማጽደቅና አዳዲስ ባለአክስዮኖችን መቀበል፤
3.4 የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ. የ2025/26 ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ ፤
3.5 የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ. የ2025/26 ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥ ፤
3.6 ከዚህ በላይ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
3.7 እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ መቀበልና ገለልተኛ እንዲሁም ሌሎች የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መምረጥ፤
3.8 በ2018 (እ.ኤ.አ. 2ዐ25/26) በጀት ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
3.9 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ወርኃዊ አበልና ዓመታዊ ክፍያ መወሰን፤
4.ማሳሰቢያ
4.1 በጉባኤው ላይ ለመገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሰረት ጉባኤው ከሚካሄድበት ቀን አስቀድሞ ባሉት ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 2185 በሆነውና ቦሌ ድልድይ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የአክስዮን አስተዳደር ክፍል በመገኘት የውክልና ፎርም/ቅጽ በመሙላት ተወካይ በመወከል ወይም፤ በስብሰባው ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ማስረጃ ያለው ተወካይ ዋናውን እና አንድ ፎቶ ኮፒ በጉባኤው ዕለት ይዞ እንዲቀርብ በማድረግ በወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡ ፡ ሆኖም አንድ ባለአክስዮን መወከል የሚችለው አንድ ተወካይ ብቻ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
4.2 የአክስዮን ማህበሩ ባለአክስዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ በሚመጡበት ጊዜ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ኮፒ መያዝ አለባቸው፡ ፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውን የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው የማህበሩ ባለአክስዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ( ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
4.3 የባንኩን እ.ኤ.አ. የ2025/26 ዓመታዊ ሪፖርትና የዳይሬክተሮች ቦርድ የጥቆማ እና የምርጫ አፈጻጸም ፖሊሲ እና መመሪያ ከባንኩ ድረገጽ ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የብርሃን ባንክ አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ
Tel +251 116 18 57 22 / +251 116 18 57 32 / +251 116 63 20 83
Fax +251 11 662 3431
E-mail info@berhanbanksc.com / www.berhanbanksc.com
P.O.Box 387 Code 1110, Addis Ababa,Ethiopia