- ብርሃን ባንክ ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. “ የስኩል ፔይ ሲስተም ” አሰራርን መግለጫ ለምስጠት በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ጥሪ ከተደረገላቸው 40 ተጋባዥ እንግዶች መካከል 39ኙ የተገኙ ሲሆን የግል ትምህርት ቤት ባለቤቶች ፣ የከፍተኛ የትምህርት ተቋም ተወካዮች ፣ በጎንደር ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች እና ምክትል ሃላፊዎች ፣ በተገኙበት በሮዚዮ ሆቴል ገለጻው ተከናውኗል።
- የባንኩ ተ/ም/ፕ/ ኦፕሬሽን አቶ ሚሊዮን ዘለቀ ፣ ማርኬቲንግ እና ኮሚኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ግሩም ታሪኩ ፣ ዲጂታል ፋይናንሲንግ ሰርቪስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈዬራ ኢጀታ ፣ የሰሜን ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ጌታነህ በተገኙበት የእንኳን ደህና መጣችሁ መክፈቻ ንግግር በተ/ም/ፕ የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም የዲጂታል ፋይናንስ ዳይሬክተር ሰፊ ገለጻ ስለ ሲስተሙ ሰጥተዋል። በመቀጠልም ከተጋባዥ እንግዶች ጋር ስለ ሲስተሙ ያላቸውን ጥያቄ በማንሳት ሰፊና ጥልቅ ውይይት ተካሂዷል። በመጨረሻም የጎንደር ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ይሄንን ሲስተም ለማስተዋወቅ ወደ ክልሉ በመምጣቱ አመስግነው ይሄንን ሲስተም ሁሉም የትምህርት ተቋማት መጠቀም ቢጀምሩ ጠቀሜታውን በመጥቀስ ሃብት የማሰባሰብ ሂደቱ እንደሚቀላጠፍ እንዲሁም በሲስተም ላይ የተመረኮዘ አሰራር ቀዳሚ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል። የትምህርት ቤት ባለቤቶችም የትምህርት ዘርፉ ላይ ትኩረት በመስጠት ይሄንን አይነት ጠቃሚ ስራ በመሰራቱ ምስጋና አቅርበዋል።
- በመጨረሻም የትውውቅ እና የእራት ግብዣ ፕሮግራም ተካሂዷል።