ብርሃን ባንክ ለማህበራዊ ኃላፊነቱ ቅድሚያ ይሰጣል!

ባንካችን ብርሃን ባንክ፣ የነህምያ ኦቲዝም ሴንተር “ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ቀን”ን አስመልክቶ ያዘጋጀውን የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እስፖንሰር በማድረግ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የተገኙ ባለሙያዎችና እንግዶች እንደገለጹት፤ ኦቲዝም ያለባቸውን ልጆች በትክክለኛ መረጃ መደገፍና ከአድልዎ ነፃ የሆነ አካባቢ መፍጠር የሁላችንም ድርሻ ነው። ብርሃን ባንክም እነዚህን ውድ ልጆች እና ወላጆቻቸውን በማገዝ የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል።
ወደፊትም መሰል በጎ ተግባራትን በመደገፍ አብሮነታችንን እናጠናክራለን።
ብርሃን ባንክ – የብርሃ ጉዞውን ቀጥሏል