በመርሃግብሩ ላይ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ግሩም ጸጋዬ፤ የባንኩ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ በካሎን ጨምሮ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን መሪዎች እና ባለሞያዎች ተገኝተዋል፡፡
የምስጋና መርሃግብሩ የካቲት 7ቀን 2015ዓ.ም አብረውት ከሚሰሩ የተለያዩ የሚዲያ አካላት ጋር በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል፡፡
የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ግሩም ጸጋዬ በዕለቱ ባደረጉት ንግግር፤ ከባንኩ ጋር አብረው የሚሰሩ የመገናኛ ብዙሃንን አመስግነዋል፡፡
በተጨማሪም የባንኩን ራዕይና ተልዕኮ ያብራሩ ሲሆን፤ በቀጣይም ሚዲያዎቹ ይህንኑ በይበልጥ እንዲያንጸባርቁ ጠይቀዋል፡፡