ብርሃን ባንክ የ 2022/23 የግማሽዓመት የማኔጅመንት ስብሰባውን አካሂዷል፡፡

ብርሃን ባንክ የ 2022/23 የግማሽ ዓመት የማኔጅመንት ስብሰባውን ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም የባንኩ ፕሬዝዳንት፤ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፤ የዋናው መስሪያቤት የመምሪያ ሀላፊዎች  ፣ እንዲሁም የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች በተገኙበት በስካይ ላይት ሆቴል አከናውኗል፡፡

በዕለቱም በመጀመሪያ የባንኩ የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም በዝርዝር ቀርቦ  ሰፊው ውይይት ተደርጎበታል፤በመቀጠልም የሰው ሃብት አቅጣጫ ስራት (human capital strategy) ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፤ በመቀጠልም ለቀጣይ ቀሪ ስድስት ወራት የባንኩን እቅድ ቀርቦ በቂ ውይይት ተደርጎበታል፤ የባንኩ ዲጂታል ሚድያ መግለጫ ቀርቧል፡፡ በመጨረሻም የባንኩ ፕሬዝዳንት የቀጣይ 6 ወራት አቅጣጫ እና መመሪያ አቅርበው ስብሰባው ተጠናቋል፡፡