ብርሃን ባንክ ሐምሌ 12 እና 13 ቀን 2016 ዓ.ም ዓመታዊ የስራ አመራር ስብሰባውን በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል፡፡ ስብሰባው የባንኩን የ2023/24 በጀት አመት አፈፃፀምንና የ2024/25 በጀት ዓመት ዕቅዶችን ለመገምገም እንዲሁም የእርስበርስ ትብብርን ለማሳደግ ያለመ ነበር፡፡ በወቅቱም የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡት የዕውቅናና የማበረታቻ ሽልማት የመስጠት ስነስርዓት ተከናውኗል፡፡ ስብሰባው ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት አመት የተመዘገበውን አመርቂ ውጤት በማድነቅ እና ለወደፊት ያለውን ቁርጠኝነት በማጠናከር የበለጠ ድልና ስኬቶችን ለማስመዝገብ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡