ብርሃንባንክ በሀገራችን የመጀመርያውን የ’ኤምፖስ’ ማሽንበ ስራላይ አዋለ!!!

ብርሃን ባንክ ከሳንቲምፔይ  ፋይናንሻል ሶሉሽን ጋር በጋራ በመሆን  የመጀመርያ የሆነውን የኤም ፖስ ማሽን ለተጠቃሚዎች በስራ ላይ አውሏል።

ባንካችን ያስጀመረው ይህ የኤም ፖስ ማሽን ለታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች እና የዲጂታል ደረሰኝ ለሚፈልጉ ለተለያዩ  አነስተኛ ቢዝነሶች መዋል የሚችል ነው።

እነዚህ ማሽኖች ለአጠቃቀም እና ለአያያዝ እጅግ ቀላል ከመሆናቸው በላይ የኔት ወርክ ፍጥነታቸው ቀድሞ በገበያ ላይ ካሉት የፖስ ማሽኖች ጋር ሲነጻጸር  ከፍተኛ ፍጥነት ያለው  ስለሆነ ተመራጭ  በመሆን በተሻለ የአገልግሎት ተደራሽነት በከተማችን ውስጥ በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ  ላይ ለተሰማሩ እና ለሌሎችም  በማሰራጨት ላይ እንገኛለን፡፡

#ብርሃን_ባንክ

እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!