ብርሃን ባንክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ለሚያስገነባው ህንፃ የአርኪቴክቸራል ዲዛይን ጨረታ አውጥቶ አሸናፊውን ያስታወቀ ሲሆን ሁሉም ለውድድር የቀረቡ ዲዛይኖች ለህዝብ ዕይታ የሚቀርቡበት ኤግዚቢሽን በወላይታ ጉታራ ሆቴል ቱሪዝም እና ስልጠና ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል፡፡

አውደ ርዕዩ የብርሃን ባንክ የደቡብ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ኤርሚያስ ግርማ፤ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን አለማየሁን ጨምሮ ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ የተጀመረ ሲሆን ከሰኔ 22 እስከ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በወላይታ ጉታራ ሆቴል ቱሪዝም እና ስልጠና ማዕከል ለህዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ በመሆኑም በወላይታ እና አከባቢው የምትገኙ ደንበኞቻችን ለሚቀጥሉት ተከታታይ 7 ቀናት የሚቆየውን ኤግዚቢሽን እንድትመለከቱ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡