የብርሀን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ አርኪቴክቸራል ዲዛይን ውድድር የህዝብ አውደ ርዕይ ተከፈተ!

የብርሃን ባንክ የዋና መስሪያ ቤት ህንጻ አርኪቴክቸራል ዲዛይን ውድድር የቀረቡ ዲዛይኖች ለህዝብ ዕይታ የሚቀርቡበት ኤግዚቢሽን እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ኤግዚቢሽኑ በዛሬው ዕለት የባንኩ የስራ አመራሮች በተገኙበት በይፋ የተጀመረ ሲሆን ከግንቦት 5 እስከ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ልደታ አካባቢ በሚገኘው ህንፃ ኮሌጅ ጊቢ ውስጥ ለህዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

በመሆኑ ክቡራን ደንበኞቻችን ለሚቀጥሉት 15 ቀናት የሚቆየውን ኤግዚቢሽን እንድትመለከቱ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡