በኢትዮጵያ ዘመናዊ የትምህርት ቤት ክፍያ ሥርዓትን በመጀመር የመጀመሪያው ቀዳሚ ባንክ የሆነው ብርሃን ባንክ ፣ አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ እና ፈጣን ለማድረግ አሁን ደግሞ አዲስና አማራጭ የክፍያ ሂደት ይዞ ቀርቧል ።
በአሁኑ ወቅት ከ1,000 በላይ ትምህርት ቤቶች በስርዓታችን ውስጥ ተካተው አገልግሎት እየሰጡ በሚገኙበት በዚህ የ«ብርሃን ስኩል ፔይ» (Berhan School Pay) ፣ ደንበኞች ከዚህ ቀደም ከነበሩት የክፍያ አማራጮች በተጨማሪ አሁን በቀጥታ በቴሌብር (telebirr) መተግበሪያ በኩል ክፍያ መፈጸም እንደሚችሉ ባንኩ በደስታ ይገልጻል ።ወላጆች እና ተማሪዎች የወረፋ እና የጊዜ መባከን ሳይኖርባቸው፣ የተማሪውን መክፈያ ኮድ (Payment Code) ወይም ስልክ ቁጥር ብቻ በመጠቀም በጣም በአጭር እና ፈጣን መንገድ ክፍያቸውን ማጠናቀቅ ይችላሉ ።
የክፍያ አማራጮች
አዲሱ የቴሌብር ትስስር እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ወላጆች አሁንም በተለመዱት የባንካችን ዲጂታል አማራጮች ክፍያ መፈጸም ይችላሉ ፦
1. በብርሃን ሞባይል ባንኪንግ (በመተግበሪያ/App እና በUSSD *881#)
2. በኢንተርኔት ባንኪንግ
3. በሁሉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፎች
በቴሌብር መተግበሪያ ክፍያ የሚፈጸምበት ቅደም ተከተል (
ክፍያዎን በቴሌብር ለመፈጸም እነዚህን ይከተሉ ፦
1፦ የቴሌብር (telebirr) መተግበሪያን በስልክዎ ላይ ይክፈቱ ።
2፦ ከክፍያ አማራጮች (Payment) ውስጥ “Education Fee” የሚለውን መርጠው “Berhan School Pay” የሚለውን ይጫኑ ።
3፦ ክፍያውን በተማሪው የመክፈያ ኮድ (Payment Code) ወይም በስልክ ቁጥር (Phone Number) ለመፈጸም ከተቀመጡት አማራጮች ውስጥ አንዱን ያስገቡ፤ በመቀጠልም “Next” የሚለውን ይጫኑ ።
4፦ በመቀጠል በስክሪኑ ላይ የመጣውን የተማሪውን ስም፣ የትምህርት ቤቱን ስም እና የክፍያ መረጃ ትክክለኛነት ያረጋግጡ፤ ከዛም “Next” የሚለውን ይጫኑ ።
5፦ የቴሌብር ሚስጥር ቁጥርዎን (PIN) አስገብተው በማረጋገጥ ክፍያውን ያጠናቁ፤ የክፍያ ማረጋገጫ ደረሰኝዎንም (Receipt) ወዲያውኑ ያግኙ ።
ብርሃን ባንክ
እንደስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!
