ብርሃን ባንክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ለሚያስገነባው ህንፃ የአርኪቴክቸራል ዲዛይን ጨረታ አውጥቶ አሸናፊውን ያስታወቀ ሲሆን ሁሉም ለውድድር የቀረቡ ዲዛይኖች ለህዝብ ዕይታ የሚቀርቡበት ኤግዚቢሽን በወላይታ ጉታራ ሆቴል ቱሪዝም እና ስልጠና ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል፡፡