ብርሃን ባንክ የ150 በመቶ ትርፍ እድገት አስመዘገበ
ብርሃን ባንክ 15ተኛ መደበኛ እና 6ተኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ሐሙስ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ አካሄደ፡፡ በጉባኤው ላይ የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ኤሊጎ ለገሰ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2024 የተጠናቀቀውን የባንኩን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለባለአክሲዮኖች አቅርበዋል፡፡ አቶ ኤሊጎ በሪፖርታቸው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የባንኩ የሥራ ክንውን በተለይ ከትፋማነት አንጻር በኢንዱስትሪው …