ብርሃን ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንስ ተቋማት መናሀሪያ በሆነው ሜክሲኮ አካባቢ በ 5400 ሜ.ካ ቦታ ላይ የዋና መስሪያቤት ህንጻ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ፡፡
የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነስርዓቱ አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገ/ሥላሴ፤የብርሀን ባንክ የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጉማቸው ኩሴ፤ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ግሩም ጸጋዬን ጨምሮ የባንኩና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ፤ ባለ አክሲዮኖች እና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡ አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገ/ሥላሴ በስነ ስርአቱ ላይ ልክ እንደስሙ ባንኩ በብርሀን ፍጥነት ህንጻውን ገንብቶ ማጠናቀቅ አለበት …